Story Image

የቃኘው የድል ጉዞ

ቃኘው የእግር ኳስ ክለብ የአዲስ አበባን ከፍተኛ ዲቪዥን ሰንጠረዥ በአስደናቂ ሁኔታ 18 ነጥቦችን ሰብስቦ የውድድሩን የመጀመሪያ ዙር በመሪነት አጠናቁአል።

ከአንድ  ሽንፈት እና ስድስት አስደናቂ ድሎችን በመጎናፅፍ መሪነታችንን ያጠናከሩልንን 22 ጎሎችንም በማስቆጠር 7 ጎሎችን በማስተናገድ የቡድኑን የማጥቃት ብቃት እና የመከላከል ጥንካሬ አሳይተዋል።

ደጋፊዎችም በፍፁም የበላይነት የተሞላውን ጨዋታዎቻችን አድናቆትን እና ደስታን በደጋፊ ዘንድ አስገኝቶልናል፣ ከግብ ፊት ለፊት ያላቸው አስተማማኝ የአጨራረስ ብቃት እና የተቀናጀ የቡድን ሥራ በማጣመር፣ የውድድሩ ዋነኛ ተቀናቃኝ በመሆን ስሙን በደማቁ ፅፏል።

የዚህ ስኬት ዋናነኛ ምክንያት የቡድኑ የማያቋርጥ የሥራ ትጋት፣ የተጫዋቾች ያላሰለሰ ሳምንታዊ የስልጠና ዝግጅቶችን በአግባቡ በመተግበር በአሰልጣኞች የተዘጋጀውን ስትራተጂካዊ ዝግጅቶችን በማረግ ይሳተፋሉ።

የስልጠናው አካል የሚያተኩረው ብድኑ ያለውን  ጠንካራ መንፈስ በአካል ብቃት፣ በታክቲካል ግንዛቤ እና በቡድን ቅንጅትን በይበልጥ መገንባት ላይ ነው።

ቃኘው ለሁለተኛው ዙርም ዝግጅቱን አላቋረጠም። የአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዤዎንን ለማሸነፍ እና ወደ ብሔራዊ ሊግ በመቀላቀል የብድኑንም ግብ ለማሳካትም ቆርጠው ተነስተዋአል። በራስ መተማመናቸው እየጨመረ ያሉት ተጫዋቾቻችን ምክንያት ድልን በተከታታይ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል።

ምኞትን ወደ ተግባር በመቀየር ላይ ያለው ክለባችን ለወደፊቱ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለመቀየር ተስፋ ያረጋል።