Story Image

ጂንካ እና አዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ጉዞ

ቃኘው! የመጀመሪያ ትልቁን የስኬት መሰናክል አልፈናል። 
 
ቡድናችን በአስደናቂ ሁኔታ 31 ነጥብ በማሰባሰብ የአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ምድብ ሀን በሰንጠረጁ አናት ላይ አጠናቋል።
 
በተመሳሳይ ጊዜ ፣ ከተማችንን በጂንካ የመወከል ክብርም አግኝተናል። ለክልል ሻምፒዮናም ከሌሎች አራት የአዲስ አበባ ክለቦች ጋር እንሳተፋለን። ቡድናችንም ያሳየውን ጠንካራ የሊግ አቋም ወደ ጂንካ ይዞ በመሄድ የማሸነፍ መንፈሱን ለማስቀጠል ቆርጠን ተነስተናል። ለሁለቱም ውድድሮች በአንዳይነት የአሸናፊነት መንፈስ እና ሙሉ ጉልበት ሰንቀን ለጉዞ ተዘጋጅተናል።

ይህን የድል ጉዞ የሚገርም ድንቅ አቋም እና  ችሎታ እያሳየን ይገኛል። በዚሁ የውድድር ዘመንም በምድብ ሀ አስር ጊዜ በማሸነፍ አንድ ጊዜ ብቻ ሽንፈት እና አቻ  አስተናግደናል።

የዚህም አስደናቂ ወጤት ዋነኛ ምክንያቶች እያንዳንዱን ተጫዋቾች አሰልጣኞች እና የቡድን አባሎች የሚያሳዩት ታታሪነት ፣ ቁርጠኝነት እና የትግል መንፈስ ዋነኛ ማሳያ ነው።

ከጂንካ ውድድር በኋላ ለሚጠብቀን ወሳኝ የሊግ የጥሎ ማለፍ ውድድር ምድብ ሀ'ን በአንደኛነት ማጠናቀቃችን  ተከትሎ ከምድብ ለ ሁለተኛ ጋር ያገናኘናል።
እንደ ቡድን ያለንበትን ጥሩ ደረጃ እና ድንቅ ቅርፅ ወደ መጨረሻዎቹ ጦርነቶች እንድንገባ ትልቅ ስንቅ ይሆነናል።
የዚ አመት የመጨረሻው ግብችንም በጂንካ በሚካሄደው ውድድር ዋንጫ ማንሳት ወይም ወደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ከሚያድጉት አራቱ ክለቦች ውስጥ አንዱ መሆን፣ከዛም ባለፈ የአዲስ አበባን ከፍተኛ ዲቪዚዎን ዋንጫ ማንሳት ይሆናል።
ይህ ከባድ ግን አስደሳች ጉዞ ይቀጥላል።